
በመልካም አስተዳደርና መሰል ዘርፎች ላይ ከሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋምና ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ጋር በመተባበር ለግማሽ ቀን የቆዬ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
በውይይት መድረኩ ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ስመኝ ውቤ እና የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም በመልካም አስተዳደር፣ በሰብዓዊ መብትና ተያያዥ ዘርፎች ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በተሰጠው ስልጣንና ተግባር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፍ እና የመንግስት ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት መስራት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የጋራ ዓላማ ያላቸውን ሴክተር መስሪያ ቤቶችንና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማቀናጀት ውጤታማ ተግባራትን እንዲያከናውኑ ለማስቻል ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጋር በመተባበር በመልካም አስተዳደርና መሰል ዘርፎች ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከተቋሙ ጋር በቅንጅትና በትብብር ለመስራት የሚችሉበትን አሰራር ለመፍጠር የተደረገ የውይይት መድረክ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ላለፉት 20 ዓመታት በህዝብ አስተዳደር በኩል የሚቀርቡ የመልካም አስተዳደር አቤቱታዎችን በመቀበል ፣ በመመርመርና የመፍትሄ ሀሳቦችን በማቅረብ እንዲሁም ተቋማት የመልካም አስተዳደር መርሆችን አክብረው እየሰሩ መሆኑን የመቆጣጠር ስራ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው ተቋሙ በመልካም አስተዳደር ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በአጋርነትና በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋት ዘርፉ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጣ በጋራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው የሚመለከታቸው የፌደራል ባለድርሻ አካላት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር የሚያደርጉት ቅንጅትና ትብብር የመንግስት ተቋማት ተልዕኳቸውን በትክክል ለመወጣት እንደሚያስችላቸው ጠቁመው የዘርፍ ተቋማትም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ትርጉም ያለው ውጤት እንዲያመጡ የማሳተፍና የመደገፍ ስራ ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ከእቅድ አንስቶ እስከ አፈጻጸም በጋራ መስራት የሚቻልባቸውን ሴክተር ተኮር የትብብር መድረኮች እንዲደራጁና ወደስራ እንዲገቡ ማድረግ በትኩረት የሚሰራበት መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ
ለዚህም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣ ህብረቶችና ኔትዎርኮች የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው መቀጠል እንዳለባችው ገልፀዋል።
Tagline
Long headline on two lines to turn your visitors into users
Change the color to match your brand or vision, add your logo, choose the perfect layout, modify menu settings, add animations, add shape dividers, increase engagement with call to action and more.


Tagline
Long headline on two lines to turn your visitors into users
Change the color to match your brand or vision, add your logo, choose the perfect layout, modify menu settings, add animations, add shape dividers, increase engagement with call to action and more.

