ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ጋር በመተባበር ለሠራተኞች ክፍያ የማይጠየቅባቸው የቤት ውስጥ ስራዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
ማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ ስራዎች (Unpaid Domestic Work) ይህ በቤት ውስጥ የሚከናወን ነገር ግን በገንዘብ የማይገለጽ የዕለት ተዕለት ስራዎችን ያጠቃልላል። እነዚህ ስራዎች ለቤተሰብ ደህንነት እና ማህበራዊ ደህንነት የማይቀሩ ቢሆኑም፣ ብዙውን ጊዜ በሴቶች እና በልጃገረዶች ላይ የሚወድቁ ሲሆን፣ ይህም የጾታ እኩልነትን እና ኢኮኖሚያዊ እድሎችን በተመለከተ ችግሮችን ያስከትላል።
በስልጠናው ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንደተናገሩት የሰራተኞቻችንን አቅም ለመገንባት የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ በመግለፅ ቀጣይነት እንደሚኖረውም አንስተዋል፡፡
አክለውም የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ለሃያ ዓመታት በሴቶች ላይ እየተሰሩ ያሉት ስራዎች የሚበረታቱ መሆኑን አንስተው የሴቶችን እኩልነት ሴቶችን በማንቃት ሴቶችን በማደራጀት ያላቸውን እምቅ አቅም እንዲጠቀሙ እንዲሁም በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ እንዲጎለብት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ በመሆናቸው ዋና ዳይሬክተሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ሌላው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተለያየ ዘርፍ የተደራጁትን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመመዝገብ የመቆጣጠር እና የመደገፍ ስራዎችን እንደሚሰራ በመግለፅ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን አቅም ለማሳደግ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ እያገዛቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡
በተለይ በሴቶች በወጣቶችና በህፃናት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች እያደረጉ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ሴቶች የሚገባቸውን ክብር በመስጠት ማግኘት የሚገባቸውንም እንዲያገኙ በማድረግ የበኩላችንን ሀላፊነት መወጣት አለብን ሲሉ ተናግረወ፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ዳይሬክተር ሳባ ገ/መድን እንዳሉት ማህበሩ ትኩረቱን በሴቶች ላይ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በዋናነት በሴቶች እኩልነት እንዲሁም ሴቶችን በማህበራዊ፡ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ላይ ያላቸው ተሳትፎ ከማጎልበት አንፃር ማህበራቸው ሴቶችን በስልጠናዎች የማብቃት ስራዎችን እየሰራ እነደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ማህበራቸው ለሃያ ዓመታት ከአስር በላይ ማህበራትን በማቀፍ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ በመግለፅ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋርም በመተባበር ለሰራተኞች ስልጠናዎችን እንደሰጠ ተናግረዋል፡፡