የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ የበጎ ፈቃድ እና የበጎ አድራጊነት ባህልን በህብረተሰቡ ውስጥ ለማስረጽ በተለያዩ ዩኒቨርሶቲዎች እና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሚገኙ ተማሪዎች የግነዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
የበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ በእንጦጦ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በበጎ ፈቃድ ዙሪያ ለሚሰሩ ተማረሪዎች በበጎ ፈቃደኝነት ምዝገባ ዌብ ሳይት አጠቃቀም (VIMS) እና በበጎ ፈቃደኝነት ዙሪያ ለግማሽ ቀን ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር መሪ ስራ አስፈጻሚ ቡድን መሪ ወ/ሮ ሽልማት መርሻ ለሰልጣኞች ያስተላለፉት መልዕክት ባለስጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ 1113/2011 በተሰጠው ስልጣን መስረት የበጎ ፈቃድ እና የበጎ አድራጊነት ባህልን በህብረተሰቡ ውስጥ ለማስረጽ በዩኒቨርሲቲዎች እና በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሚገኙ በበጎ ፈቃድ ላይ ለተሰማሩ ተማሪዎች ስልጠናዎችን እየሰጠ እንደሚገኝ በመግለጽ ይህንንም አጠናክሮ ለማስቀጠል በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ የበጎ ፈቃደኝነት ክበብ እንዲቋቋም ለማድረግ ትኩረት አድርጎ የሚሰጥ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በበጎ ፈቃደኝት ላይ የሚሳተፉ አካላት በፍላጎታቸውና በክህሎታቸው ላይ እንዲሁም በእድሜያቸው ተመርኩዘው የተለያዩ ሚናዎችንና ፕሮጀክቶችን የመሞከር እድል እንዲያገኙ የሚረዳ ሲሆን ዋንኛ ዓላማው በበጎ ፈቃድ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች የማህበረሰብን ስሜት ይረዳሉ፣ ማህበራዊ ክህሎቶችን ያዳብራሉ ጠቃሚ የሆኑ ችሎታዎችን ያገኛሉ የሥራ ዕድሎች ይፈጠራሉ፣ በሕይወታቸው ውስጥ አስደሳች ነገሮች ይፈጠራሉ፣ አዳዲስ ክህሎቶች እና እውቀት እንደሚያገኙ በስልጠናው ላይ ተገልጧል።


