• ግብዐቶች
  • ኩነቶች
  • ዓመታዊ ሪፖርቶች
  • መልቲሚዲያ
  • Call For Paper
  • ማስታወቂያዎች
  • አግኙን
  • English
ACSO
  • ሲ.ማ.ድ
    • ለአዲስ የሲ.ማ.ድ
      • አዲስ ሲ.ማ.ድ ማስመዝገብያ መስፈርቶች
    • የተመዘገቡ የሲ.ማ.ድ
      • ሀገር በቀል
      • የውጪ ሀገር
      • የሙያ ማኅበራት
      • የብዙሃን ማህበር
      • የበጎ አድራጎት ኮሚቴ
      • ቦርድ መር
      • በክልል የተመዘገቡ
    • ስለ ሲ.ማ.ድ.ባ የምርመራ ስልጣን
      • ባለስልጣኑ ምን ሊመረምር ይችላል
      • ባለስልጣኑ መመርመር የማይችላቸው ጉዳዮች
    • ሲ.ማ.ድ ስለመቆጣጠር
      • ሲ.ማ.ድ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች
      • ሲ.ማ.ድን ስለመቆጣጠሪያ
      • የቅሬታ/የስጋት ምክንያቶች/አይነቶች
  • ስለ ባለስልጣኑ
    • መረጃ
      • ስለ ባለስልጣኑ
      • የባለስልጣኑ ስልጣንና ተግባራት
      • የተቋም አደረጃጀት
      • ሕጎች
      • አጋሮች
    • የስራ ክፍሎች
      • ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቢሮዎች
      • መሪ ስራ አስፈፃሚ
      • ስራ አስፈፃሚ
    • ለማህበረሰብ
      • መግለጫዎች
      • ክፍት የስራ እድሎች
  • ዜና
  • የበጎ ፈቃደኞች መመዝገቢያ
    • ለበጎ ፈቃደኞች
    • ለአጋር ድርጅቶች
    • ለበጎፈቃደኛ አስተባባሪዎች
  • ቅሬታ ማስተናግጃ
  • ኢ-ሰርቪስ
  • ግብዐቶች
  • ኩነቶች
  • ዓመታዊ ሪፖርቶች
  • መልቲሚዲያ
  • Call For Paper
  • ማስታወቂያዎች
  • አግኙን
  • English

12ኛው የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልልና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የጋራ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡

12ኛው የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የክልልና የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የጋራ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡

በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጨምሮ በርካታ የመንግስት እና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በመክፍቻ ንግግራቸው እንዳሉት መንግስት በርካታ ፈተናዎችን እያለፈ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከለውጡ በኋላ በመንግሥትና በግል ባለሃብቱ የማይሸፈኑ የልማት ሥራዎችን በመተካት ወሳኝ ሚና እየተወጡ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
ሲቪል ማኀበረሰብ በሀገሪቱ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት እንዲችሉ ህግና ፖሊሲዎችን አዘጋጅቶ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱና መብቶቻቸው እንዲከበሩ አድርጓል። ሲቪል ማህበረሰቡ ለኢትዮጵያ ልማት እና ሰላም ግንባታ በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ መንግስት የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አፈ-ጉባኤው አስታውቀዋል።
Click the button
የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን በበኩላቸው የሲቪል ማህበረሰብ በሀገራችን ተመዝግበው በልማት፣ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ፣ በሰላም ግንባታ፣ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በስፋት መንቀሳቀስ የሚችሉበት አውድ መፍጠር ተችሏል ብለዋል። በቀጣይም በኢኮኖሚ ዕድገት ተጨማሪ አቅም በመሆን በማህበራዊ ልማት የነቃ ተሳትፏቸው እንዲጎለብት፤ አርዓያነት ያለዉን ተግባር በማሳየት አወንታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የባለስልጣን መስሪቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንደገለፁት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሪፎርም ሂደት ውስጥ በማለፍ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብን ኑሮ ለማሻሽል የሚየስችሉ ዘርፈ በዙ ተግባራትን ማከናወኑን ተናግረዋል። ሲቪል ማህበረሰብ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ እና በዘርፉ የተጀመሩ ሪፎርሞች መሰረት እንዲይዙ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
Click the button
በቀጣይም የሲቪል ማህበረሰብ ምክር ቤትን ጨምሮ ህግን አክብረው የሚሰሩ ሲቪል ማህበረሰብ ሁሉ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። በሁለት ቀናት ቆይታ በርካታ ርዕሰ ጉዳዬች የተነሱ ሲሆን በተለይም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ክትትል እና ቁጥጥር ለማህበረሰብ እና ለሃገር ተጠቃሚነት በሚል ርዕስ በአቶ ፋሲካው ሞላ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የክልል የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች NGO desk ላይ የሚሰሩ ሃላፊዎች የተወያዩበትን ተሞክሮ እና በቀጣይ ቢከናወኑ ብለው ያነሷቸውን ጉዳዬች ለጉባኤው አቅርበዋል፡፡
Click the button

በተጨማሪ

November 3, 2026

የኢፌደሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ አከበረ፡፡

November 3, 2026

የEthiopian Intergenerational dialogue initiative ማስጀመሪያ መድረክ ተካሄደ፡፡

November 3, 2026

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሴቶች ፎረም ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ።

ወደ ዜና ገጽ
ስለ ባለስልጣኑ

ሲ.ማ.ድ.ባ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ለመመዝገብ ፣ ለመደገፍ እና ለመከታተል የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው ፡፡

ይፈልጉ
  • እንዴት ማመልከት ይቻላል
  • አገልግሎቶች
  • ይጠይቁን

””

  • Today's visitors:206
  • Today's page views 317
  • Total visitors 93,118
  • Total page views 157,916
አድራሻ

ቸርችል ጎዳና ፣ ቴዎድሮስ አደባባይ ፣ ህብረት ኢንሹራንስ ህንጻ ከ4-8 ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ

ለመነጋገር

ኢሜል:  info@acso.gov.et

ስልክ: +251 115 582378
ስልክ 2: +251 115 582379
ፋክስ: (011) 558 1825
የፖስታ ሣጥን: 14340

© 2026 ACSO. All rights reserved

Privacy Preference Center

Privacy Preferences

Skip to content
Open toolbar Accessibility Tools

Accessibility Tools

  • Increase TextIncrease Text
  • Decrease TextDecrease Text
  • GrayscaleGrayscale
  • High ContrastHigh Contrast
  • Negative ContrastNegative Contrast
  • Light BackgroundLight Background
  • Links UnderlineLinks Underline
  • Readable FontReadable Font
  • Reset Reset