በሎካላይዜሽን ዙርያ በሀገር ደረጃ ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችሉ ስራዎች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ተባለ ፡፡
ዴቬሎፕመንት ኤክስፐርታይዝ ሴንተር (Development Expertise Center) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በኢትዮጵያ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በህፃናትና ወጣቶች ላይ በስፋት እየሰራ ያለ ድርጅት ሲሆን ዎርክ ሾፕ ኦን ሎካላይዜሽን(Work Shop on Localization) በሚል ርዕሰ ላይ ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዲሁም ለባለስልጣን መስርያቤቱ የቦርድ አባላት ስልጠና ሰጥቷል ፡፡
የውየይቱን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳሰይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግስት ባካሄደው ሪፎረም የሲቪክ ምህዳሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲሰፋ ሁኗል በማለት ዜጎችም በነፃነት ተደራጅተው መብታችውን የሚያስጠብቁበት፣ ለሀገር አስተዋፅኦ የሚያደርጉበትና የህግና ተቋማዊ ሁኔታዎችን መፍጠር የተቻለበት ነው ብለዋል፡፡ የተጀመረው የሲቪል ማህበራት ሪፎርም የበለጠ እንዲጎለብት እና ፍሬ እንዲያፈራ ቀጣይነቱን እና ውጤታማነቱን የሚያረጋግጡ ስራዎች ለይቶ ማከናዎን አስፈላጊ ነው በማለት ከዚህ አኳያ ከተከበራችሁ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር አጀንዳ አድርገን የምንወያይበት የሎካላይዜሽን ጉዳይ አንዱ እና ወሳኝ ጉዳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በአገራችን ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በቀጥታ በሰብዓዊ ድጋፍም ሆነ በልማት ስራዎች ላይ ከሚሰሩ ይልቅ የሚያመጡትን ሃብት ለአገር በቀል ድርጅቶች በማስተላለፍ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኙ የአገር በቀል ድርጅቶች ራሳቸው ስራውን እንዲሰሩ ቢያደርጉ የበለጠ ወጭ ቆጣቢ፣ ውጤታማ እና በዘላቂነት ችግርን የሚፈታ እንደሚያደርገው ይታመናል ብለዋል፡፡
በአገራችን ይህ የሎካላይዜሽን ጉዳይ አጀንዳ ተደርጎ ብዙም የተመከረበት ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚጠበቀውን ያህል ወደ መሬት እንዲወርድ ያልተደረገ በመሆኑ በሎካላይዜሽን ዙሪያ በሀገር ደረጃ ግንዛቤ መፍጠር የሚያስችሉ ስራዎችን ማከናዎን ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ቐሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሩ ባስተላለፉት መልዕክት የለውጡ መንግስታችን የመደመር እሳቤን በመከተል በሁለንተናዊ ብልፅግና ሀገራችንን እውን ማድረግ ነው ያሉ ሲሆን በዚህ ሪፎርም ውስጥም የሲቪል ሶሳዪቲውም ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል ፡፡
በቀጣይም የመንግስት አቅጣጫ በሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል ፡፡ በመጨረሻም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ቦርድ አባልና የፌደራል የህግና ፍትህ ምርምር ኢኒስቲቲዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘካሪያስ ኤርኮላ በማጠቃለያው ላይበሰጡት አስተያየት በዚህ ዎርክ ሾፕ የተወያየነው የሎካላይዜሽን ፅንስ ሃሳቦች ጠቃሚና ገንቢ ሃሳቦች ናቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራው በደንብ መስፋት እንዳለበት አክለው ማህበረሰቡ ፣የመንግስት አካላት እንዲሁም የፖሊሲ አውጪዎችም እንዲገነዘቡ ማድረግ መቻል ይኖርበታል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፍዋል።
ዴቬሎፕመንት ኤክስፐርታይዝ ሴንተር (Development Expertise Center) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት በጅማ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በወጣቶች ላይ እየሰራ ያለውን ስራ በዎርክ ሾፑ ላይ የተገኙት አባላት ጎብኝተዋል፡፡