በሃላፊነት ስሜት የሚንቀሳቀስ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ይህ የተባለው በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የተመራ ልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ደርጅቶች ምክር ቤት ጋር ባደረጉት ውይይት ነው ፡፡
በውይይቱ ወቅት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ገንቢ አስተያየትን መሰረት በማድረግ ህዝብን እና ሃገርን የሚጠቅም ጉዳይ ላይ መሳተፍ እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በበኩሉ በአዋጅ 1113/2011 እራስን በራስ የማስተዳደር ስልጣን እና ተግባርን በመጠቀም በዘርፉ የሚፈጠሩ ችግሮችን በንግግርና በውይይት የመፍታት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተመላክቷል፡፡
ከሰሞኑ በታገዱ ሶስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዙሪያ እና በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡