May be an image of 8 people, tree and grass

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የስራ እንቅስቃሴአቸውንና ለህብረተሰቡ እየሰጡ ያለውን አገልግሎት በጂንካ እና በወላይታ ሶዶ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ጉብኝት የተደረገላቸው ድርጅቶች ወርልድ ቪዥን÷ ኤም ኤስ ኤፍ ቤልጄም÷ ዩሪያአዲስ እንዲሁም ጠረጴዛ ልማት ማህበር ናቸው፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህብረተሰብን የላቀ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰሩ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን የኢፌደሪ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሃን በጉብኝቱ ወቅት ገልፀዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍሲካው ሞላ በበኩላቸው የጠረጴዛ ልማት ማህበር እያከናወነ ያለው ስራ ከአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አንፃር አበረታች መሆኑን አንስተዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ከመገንባት አንፃር ጉልህ ሚና እንዳለው በመግለፅ የኢትዮጵያ ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ላይ በንቃት መሳተፍ አለባቸው ብለዋል፡፡ የድርጅቶቹ ሀላፊዎች እንዳሉት በተደረገው ጉብኝት መደሰታቸውን በመግለፅ ይበልጥ በስራቸው ላይ ተነሳሺነትን እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡