አቶ ተንኳይ ጆክ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር እና የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ከለውጡ በኃላ በክልሉ በርካታ የሪፎርም ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በተለይም ሰው ተኮር የሆኑ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
May be an image of 5 people, grass and tree
አየበጎ ፍቃድ ስራዎች አንድነትን የሚፈጥሩ በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ያሉት ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በክልሉ በበጎ ፍቃድ ስራ ላይ በመሰማራታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ በንግግራቸው እንደገለጹት ከመደበኛ ስራ በተጨማሪ በማህበራዊ ሃላፊነት ዙሪያ በባለፉት ዓመታት ጀምሮ የፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትን በማስተባበር በርካታ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን መስራታቸውን አስታውሰዋል፡፡  ያይዘውም በዘንድሮ በጀት ዓመት በጋምቤላ ክልል በአምስት የበጎ ፍቃድ ዘርፎች ማለትም ለችግረኟ ቤተሰብ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣የአረንገዴ አሻራ መርኃ ግብር፣ የአቅመ ደካማ ሰዎችን ቤት እድሳት፣ለወጣቶች በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ስልጠና መስጠትና የከተማ ጽዳት መርሃ ግብሮች ተካተዋል፡፡ በዚህም መሰረት ለ625 ችግረኛ ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ከአስር ሺህ በላይ አስራ አንድ አይነት ዝርያ ያላቸው ለማህበረሰቡ ኢኮኖሚዯዊ ጠቀሜታ የሚሰጡ ችግኞችን መትከል፣ ለአምስት አቅመ ደካማ ሰዎች የቤት እድሳት ስራ እና የከተማ ጽዳት ስራ የተሰራ ሲሆን በቀጣይም ፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ችግኞችን መንከባከብ ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ በሂደቱ World Vision Ethiopia፣Action Against Hunger, Goal Ethiopia- house reinnervation, Mary Stops International Ethiopia, Amref health Africa- house reinnervation እና Ethiopia CSO Council የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።