
በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ስር የሚተዳደርው የሐረር አግሮ-ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናችውን 104 ተማሪዎች ትናንት አስመረቋል። የኢፌዴሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት አገር አቀፍ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬ እና ሌሎች ተጋባዥ እንገዶች በተገኙበት በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቌል። በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከትምህርት ተደራሽነት በተጨማሪ በርካታ አገር አቅፍ የልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የአገራችን ህዝብ ሁለንተናዊ የልማት አጋር እንደሆነ ተናግረዋል። የሰዎች ለሰዎች ድርጅት አገር አቀፍ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬ በበኩላቸው ድርጅቱ በኢትዮጵያ በርካታ የልማት ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በተለይም የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳድግ ሰፊ ስራዎችን በመስራት ይገኛል ብለዋል። በዚህም የጀርመን ሕዝብና መንግስት ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ከተመሰረተ ከ30 አመታት በላይ ያሰቆጠረው የሐረር አግሮ-ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ እስካሁን ከ3800 በላይ የበቁ ባለሞያዎችን በዲፕሎማና ዲግሪ አስመርቌል። በዚህ በጀት ዓመት ተመራቂዎቹ የሰለጠኑት በማኑፋክቸሪንግ፣ አውቶሞቲቭ፣ ኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ነው።

