የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች ተሳታፊ የሆኑበት ተቋማዊ የንባብ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋማችን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደገለጹት ይህ በተቋም ደረጃ የተጀመረው የማንበብ ባህል በጣም ጠቃሚ እና አስተማሪ መሆኑን ገልጸው ከዚህ የበለጠ የንባብ ቀን አባላት በስራ እና በስነምግባር አራያ ሆነው ለሌሎች ተቋማት የምናስተላልፈው ሞዴል ተግባር እንዲሆን መስራት አለብን ብለዋል ፡፡May be an image of 1 person, newsroom and text
አያይዘውም 17ተኛው የፌደራል የመንግሥት መ/ቤቶች የሴቶች የቫሊቦል ውድድር ላይ ተቋማችን ሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆኑን ገልጸው በጨዋታ ብቃትዋና በስፖርታዊ ጨዋነትዋ የተቋማችን የበጎ ፈቃድ ዴስክ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሽልማት መርሻ የወርቅ ሜዳለያ ተሸላሚ በመሆናቸው ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የንባብ ቀን ዓላማ የሰራተኞችን የማንበብ ባህል እንዲጎለብት ለማድረግ ፣ ከተለያዩ የተቋሙ ሰራተኞች የህይወት ልምድ የሚቀሰምበት ብሎም እርስ በእርስ የሚያቀራርብ መድረክ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡