የቤኒሻንጉል ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት የሀገራችን እና የክልላችን መንግሥት በየዘርፉ የነደፏቸውን ዕቅዶች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ በማጠናቀቅ ባንድ በኩል የህዝብን ተጠቃሚነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሻገር፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሀገራችን የብልፅግና ጉዞ ስኬታማነት ተደማሪ አቅም ለመፍጠር የጋራ ርብርብ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ በዚህ የጋራ ጥረትና ርብርብ ውስጥ ደግሞ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እገዛና ድጋፍ ከፍተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ ምክንያት እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል ዘርፉ የሚመራበትን አዋጅ በማፅደቅ ተግባራዊ ማድረጋቸውን እና በእስካሁኑ ሂደት የተመዘገቡ ለውጦችም አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ የተጀመሩ የጋራ ጥረትና ርብርብ ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ በመግለጽ በዚህ ረገድ እንደመንግሥት በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር የጀመርነውን የጋራ ጥረት የበለጠ አጠናክሮ ማስቀጠል ይጠበቅብናል ሲሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል፡፡
May be an image of 9 people and dais
የኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በበኩላቸው ሁሉም የፌዴራል ሴክተር መ/ቤቶች እና የክልል መንግስታት በዘርፉ በተጨባጭ የህዝብን ችግር የሚቀርፍ ሥራ እየሰሩ ስለመሆኑ ቋሚ የግንኙነት መድረክ በመፍጠር ጭምር ተገቢውን የክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ድጋፍ ስራ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ በዚህ ጉባኤ ትኩረት ሰጥቶ ሊመከርበት የሚገባው ጉዳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አገራችን የጀመረችው የብልጽግና ጉዞ ተከታታይ ፈተናዎችን በመቋቋም ዕዳዎችን ወደ ምንዳ በመቀየር በቁርጠኝነት ወደፊት መጓዝን የሚጠይቅ ሲሆን ለተግባራዊነቱ በጋራ መቆም ወሳኝ ነው ከዚህ አንፃር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቅ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡