የስምምነት ሰነዱ ዋና ዓላማ የሲቪል ሶሳይቲ አመራር በሲቪል ሶሳይቲ አመራር ልማት ለማብቃት፣የሃሳብ ማመንጫ ማዕከል መገንባት እና እውቀትና ሽልማት መስጠትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
አቶ ዛዲቅ አብርሃ የልዕቀት ማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አጠቃላይ የማዕከሉን ርዕይ፣ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች እና በቀጣይ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት ስለሚያስችሉ ጉዳዮች ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡May be an image of 3 people and text
ሲቪል ሶሳይቲው በዚህ አጀንዳ ላይ ሲወያይ በሃገር እድገትና ልማት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው በሚል እና ዘርፉ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ተጽዕኖ የሚፈጥር ለማድረግ የራሳቸውን የልዕቀት ማዕከል መገንባት በማስፈለጉ መሆኑን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡ተቋሙ የጀመረው ሪፎርም አንዱ መዳረሻ ይህንን የሲቪል ሶሳይቲ ልዕቀት ማዕከል መገንባት ነው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ ፕሮጀክት እየተሻሻለ እና እያደገ የሚሄድ ሲቪል ማህበረሰብ መፍጠር ነው ሲሉም አክለው ገልጸዋል፡፡ ከአፍሪካ አመራር ልዕቀት ማዕከል ጋር የተጀመረውን ስራ ማስቀጠል ጠቃሚ በመሆኑ ሲቪል ማህበረሰቡን ያሳተፈ ኮሚቴ ተዋቅሮ ተግባራዊ መሆን ይኖርበታል ሲሉም ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡
በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የዛሬው ውይይት ስትራቴጂክ ትብብር የሚፈጥር ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ሰባት ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ሁለቱ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣ እና ከአፍሪካ ልዕቀት አካዳሚ የተውጣጣ ዘጠኝ ኮሚቴዎች ተዋቅሮ የዕለቱ ፕሮግራሙ ተጠናቋል ፡፡