የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለተቋሙ ሰራተኞች የተቋሙን ስትራቴጂያዊ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በሚመለከት ስልጠና ሰጠ፡፡
May be an image of 1 person and text
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተቋሙን የ10 ዓመት ስትራቴጂያዊ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በሚመለከት ለሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች በዙር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ በስልጠናው ላይ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የብቃትና ሰው ኃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጌታቸው ለሰልጣኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዓለም ዓቀፍ አማካሪዎችን በማሳተፍ ያዘጋጀውን የ10 ዓመቱን የስትራቴጂያዊ ትራንስፎርሜሽን እቅድ ቀደም ሲል ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተለያየ መንገድ እንዲያውቁት የተደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ የተቋሙ ሰራተኞችም የትራንስፎርሜሽን እቅዱን በሚመለከት በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ስልጠናው ሊዘጋጅ መቻሉን ተናግረዋ፡፡
አክለውም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስትራቴጂያዊ ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም የተቋሙ ሰራተኛ በቂ ግንዛቤ መያዝ ያለበት በመሆኑና ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው ሊሰጥ እንደቻለ ገልጸዋል፡፡ ስልጠናው በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ቃልኪዳን መንግስቴ፣ በበጎ ፈቃድ ማጎልበትና ትብብር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሉላ ሚሊዮን እንዲሁም በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የፕሮጀክቶች አስተዳደርና አጋርነት ቡድን መሪ አቶ እንድሪስ የሱፍ አማካኝነት ተሰጥቷል፡፡ የስትራቴጂያዊ ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ዳራ እና አውድ፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ስትራቴጂክ ትንታኔ፣ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምህዳር ትንተና (PESTL and SWOT Analysis) የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ስትራቴጂክ ግቦችና አላማዎች በስልጠናው የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው፡፡