ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባዘጋጀው 3ተኛው የመንግስት እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የጋራ የምክክር መድረክ /GO-CSO Forum/ ቀደም ብሎ በክልሉ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስራን ተመልክቷል ።

በጉብኝቱ የተቋማችን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱን ጨምሮ የክልሉ የGO-CSO Forum የቦርድ አባላት እና ከተለያዩ የመንግስት ቢሮዎች የተወከሉ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በክልሉ አንድ ወረዳ ላይ ሃያ አንድ ትምህርት ቤቶች ላይ የትምህርት ቤት ምገባ የሚሰራውን Save the Children ፣በሃገራችን ሞዴል ከሆነ እና የተሟላ ግብዓት የተሟላለት የካቶሊክ የልማት ኮሚሽን ያስገነባውን ቡሽሎ የእናቶችና ህፃናት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና መቶ ሃያ ስድስት ልዪ ድጋፍ የሚሹ ህፃናትን የሚያሳድገውን ነፃነት ሚኒስትሪ ኢንክ ተጎብኝቷል።
ዋና ዳይሬክተሩ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ክልሉ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እያከናወነ ያለው ተግባር አስተማሪ መሆኑን አንስተው መሬት ላይ የተመለከቱት ስራም ውጤታማ እና የሁሉንም እርብርብ የሚጠይቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ተቋማቸውም ለማህበረሰቡ የላቀ ተጠቃሚነት ማድረግ የሚገባውን ሁሉ ያደርጋል ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።