የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ኦቲዝምን በሚመለከት ለተቋሙ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለተቋሙ ሰራተኞች በኦቲዝም ዙሪያ ለአንድ ቀን የቆዬ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ስልጠናው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከኤስ ኦ ኤስ ቺልድረንስ ቪሌጅ አዲስ አበባ ፕረሮጀክት (SOS Childrens Village Addis Ababa Project) እና ከናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በመልእክታቸው በኦቲዝም ላይ ትኩረት አድርገው ሲሰሩ የቆዩ ድርጅቶችን በጎበኘንበት ወቅት የኦቲዝም ተጠቂዎች ከፍተኛ ጥንቃቄና ተከታታይ የሆነ እገዛ እንደሚፈልጉ ተገንዝበናል፡፡ ተቋማችን ይህን ስልጠና ሲያዘጋጅ ኦቲዝምን በሚመለከት የተቋሙ ሰራተኞች ግንዛቤያቸውን ማዳበር እንዲችሉ በማለት መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው አመላክተዋል፡፡
በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጸሃይ ሽፈራው ስልጠናውን በተባባሪነት ላዘጋጁ ድርጅቶች ምስጋናቸውን አቅርበው መሰል ስልጠናዎች ወደፊትም እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል፡፡