የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ ሃላፊዎች የቴክኖ ሰርቭ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ኮሚሽንን የስራ እንቅስቃሴ ተመለከቱ፡፡

በጅማ ዞን የሚገኘው ይህ የሁለቱ ድርጅቶች የስራ እንቅስቃሴ በግብርና ስራ ላይ እና ከግብርና ጋር በተያያዘ ምርታማነትን መጨመር ብሎም እራስን በኢኮኖሚ መቻልን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ በገለጻ ወቅት ተነግሯል፡፡
ድርጅቶቹ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ አዳዲስ የግብርና ምርቶችን የማስተዋወቅ፣የአቅም ግንባታ ስልጠናና የግብዓት አቅርቦት ስራ እንደሚሰሩ ለመመልከት ተችሏል፡