ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ባለሙያዎች የኦዲት አቀራረብና የግምገማ ስርዓት ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የክትትል ግምገማና ምርመራ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሾመ ወርቁ ባስተላለፉት መልዕክት የዚህ ስልጠና ዋናው ዓላማ የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የሪፖርት አቀራረብና የግምገማ ስርዓት እንዲኖራቸው በሚያስችል ዙርያ ባለሙያው በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ታስቦ የተዘጋጀ ነው ሲሉ ገልጸዋል ፡፡
አቶ ተሾመ አክለውም ይህ ስልጠና ለተቋማችን ባለሞያዎች ጠቃሚና በስራ ገበታችን ለምንሰጠው አገልግሎት የሚሰጠው እገዛ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ ከስልጠናውም በኋላ ያገኘነውን እውቀት በነበረን ላይ በማከል የተሻለና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት የዚህ አይነት የስልጠና አጋጣሚዎች በተገቢው በመጠቀም እራሳችንን ማብቃትና ለስራ ዝግጁና ብቁ በመሆን ተገልጋዮቻችንን ማገልገል ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
Click the button