በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በየወሩ የሚካሄደው ተቋማዊ የንባብ ቀን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለ5ኛ ጊዜ በድምቀት ተካሂዷል፡፡

በዕለቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ፤ የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ጸሃፊና ተመራማሪ ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እንዲሁም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን በዕለቱ ልዩ ልዩ ስነጹሁፋዊ ስራዎች ቀርበዋል፡፡
.
በመድረኩ ላይ የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር የሆነውና በስነጽሁፍ ስራዎቹ እንዲሁም በምርምር ስራዎቹ እውቅናን ያተረፈው ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ልምድና የህይወት ተመክሮውን ለመርኃ ግብሩ ታዳሚዎች አጋርቷል፡፡
.
በተጨማሪም የባለስጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ፣ የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መሀመድ ሁሴን የተቋሙን ቤተ መጻህፍት አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል፡፡
.
የተቋሙ ቤተመጻህፍት በጥቂት መጻህፍት አገልግሎት እንዲጀምር ሲደረግ ወደፊት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘርፉን በሚመለከት በቂ የሆኑ ሰነዶች የሚገኙበትና የተቋሙ ሰራተኞችም ሆኑ ወደተቋሙ ለጥናትና ምርምር ለሚመጡ ተገልጋዮች እንዲያገለግል ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡