የባለስልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኞች በእቅድ በመመራት የተቋሙን ተልዕኮ ማሳካት አለባቸው ተባለ::

ይህ የተባለው ባለስጣን መስሪያ ቤቱ ለቡድን መሪዎች በእቅድ ዝግጅት፣ አተገባበር፣ አፈጻጸም ምዘና መመሪያ ላይ ስልጠና በሰጠበት ወቅት ነው፡፡ ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ ብቃት ያለው የሰው ሀይል ከማፍራት ጎን ለጎን በእቅድ አፈጻጸምና በውጤት የሚለካ ባለሙያ እንዲኖር ከማድረግ አኳያ በርካታ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
.
በስልጠናው ላይ የተገኙት የባለሰልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት የለውጥ ስራዎችን በመስራት ውጤታማ ተግባሮች መከናወናቸውን አንስተው ሁለተኛው ተቋማዊ ለውጥ ስራዎችን የተሻለ ለማድረግ በእቅድ መመራት መቻል አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
.
ሌላው ያነሱት አመራር ሶስት መሰረታዊ ሀላፊነቶችን አለባቸው በዋናነት በእቅድ ለመመራት እቅድ ማዘጋጀት አለበት ሁለተኛው እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ምቹ የስራ አካባቢዎች እዲኖሩ ማድረግ እዲሁም ሶስተኛው የታቀደው እቅድ እንዲተገበር ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች በአግባቡ በእቅድ በመመራት የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት ሀላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡