የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ሃገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኤግዚቭሽንን ጎበኙ፡፡

ቱሪዝም ሚኒስቴር ሃገራችን ያላትን እምቅ የቱሪዝም ጸጋዎች ለማስተዋወቅና የቱሪዝም ዘርፍ ለሃገር እድገት የሚያበረክተውን ፈርጀ ብዙ አስተዋጽኦ ለማሳየት ባዘጋጀው ሃገር አቀፍ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ኤግዚቭሽን ላይ የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ተገኝተው ተመልክተዋል፡፡