የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ክብር ላረጋውያን ግብረ ሰናይ ድርጅትን ጎበኙ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንዲሁም ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እና የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የመስዋዕትነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ክብረ አረጋውያን ግብረ ሰናይ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡ ክብረ አረጋውያን በአረጋውያን እንክብካቤና ድጋፍ ላይ የሚሰራ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ ሀገር በቀል ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው ማዕከሉ በርካታ አረጋዊያንን በመደገፍ ሙሉ እንክብካቤ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው የተመለከቱት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በማዕከሉ የሚገኙ አረጋውያንን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ አረጋውያንን ለመርዳት በሚል በጎ ርዕይ ይዘው በመነሳታቸው እና አረጋውያኑን መደገፍ በመቻላቻው የድርጅቱን መስራችና ስራአስኪያጅ የሆኑትን ወ/ሮ ወርቅነሽ ሙኔን አመስግነዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በበኩላቸው ቀኑ የመስዋዕትነት ቀን በመሆኑ አረጋውያን በዘመናቸው ኢትዮጵያ ዛሬ ለ፤ይ እንድትደርስ ትልቅ መስዋዕትነት በመክፈላቸው ሊከበሩ ይገባል ብለዋል፡፡ ድርጅቱም እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ መደሰታቸውን አያያዘው ገልጸዋል፡፡
የክብረ አረጋውያን መስራችና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሙኔ በበኩላቸው ድርጅታቸው አረጋውያንን ለመደገፍ በርካታ ጥረቶችን እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው ሆኖም ግን አረጋውያኑን ወደጤና ተቋም ለማድረስ ድርጅቱ አንቡላንስ የሌለው በመሆኑ መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበዓል ዋዜማ መጥቶ አረጋውያኑን በመጎብኘቱ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው ላደረገላቸው ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡