3ኛው ዙር ተቋማዊ የንባብ ቀን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በድምቀት ተካሄደ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን 3ኛውን ዙር ተቋማዊ የንባብ ቀን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል፡፡
ተቋማዊ የንባብ ቀኑ የተዘጋጀው የተቋሙ ሰራተኞች የንባብ ባህላቸውን እንዲዳብርና ውጤታማ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የሚያስችል መነሳሳትን በተቋሙ ሰራተኞች መካከል ለመጨመር ነው፡፡
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የአዲስ ዓመት መባቻ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለአጠቃላይ ሰራተኞች አዲሱ ዓመት የሰላም የጤና እንዲሁም የተሻለ ሰራ እምንሰራበት ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በማስተላለፍ ከንባብ ጋር በተያያዘ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት እንደዚህ አይነት ሁነቶች ተቋማዊ አንድነትና የሚያጎለብቱ እና የስራ መነሳሳትን የሚጨምሩ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል በማለት ይህን የተቋሙን አንድነት የሚያጠናክሩ ስራዎችን የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሃላፊዎችና ሰራተኞች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በተጨማሪ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፋንታዬ ኩምሳ እንዲሁም የጸረ ሙስናና ስነምግባር መከታተያ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት አቡዬ ልምድና ተመክሯቸውን አካፍለዋል፡፡
በመድረኩ ሌሎች የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች ቀርበዋል፡፡
