የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱን ጨምሮ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ሀያት በሚገኘው መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ድርጅት ተገኝተው የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
ድርጅቱ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ተመዝግቦ በአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን በርካታ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡
ይህን የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የተመለከቱት የሲቪል ማህበረሰብ ድርርቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ድርጀቱን ለመጎብኘት እድል በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከአሁን በፊት እንዳደረገው ሁሉ ወደፊትም ለድርጅቶች ድጋፍ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ድርጅቱን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

