የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ቦርድ በ14ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ቦርድ ባደረገው 14ኛ መደበኛ ስብሳባው በቅድሚያ የተወያየው የክትትል ድጋፍና ቁጥጥር መመሪያ ላይ ነው፡፡ ቦርዱ በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው የተሰጡ ማስተካከያዎች በትክክል መካተታቸውን ከተመለከተ በኋላ ተጨማሪ ግብዓቶችን በመስጠት አጽድቋል፡፡
ቦርዱ በመቀጠል የተወያየው በ2015 በጀት አመት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዋና የእቅድ አፈጻጸሞች ላይ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት አመቱ ያከናወናቸው ዋና ዋና ክንውኖች የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም የ2016 በጀት አመት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እቅድ የቀረበ ሲሆን ቀደም ሲል ለቀረበው የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ የአፈጻጸም እና ቀጥሎ ለቀረበው የ2016 በጀት ዓመት እቅድ የቦርድ አባላቱ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ቦርድ ዛሬ የጸደቀውን መመሪያ ጨምሮ 14 መመሪያዎችን ያጸደቀ ሲሆን 10 መመሪያዎች በፍትህ ሚንስቴር ቁጥር ተሰጥቷቸው ወደስራ የገቡ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ አምስት መመሪያዎች ቁጥር እንዲሰጣቸው ለፍትህ ሚንስቴር ተልከዋል፡፡
