የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ቦርን ፍሪ የተባለን የውጪ ድርጅት የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣጣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሲቪል ማህበረrሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ተመዝግቦ በእንስሳት ጥበቃ ላይ የሚሰራውን ቦርን ፍሪ የተባለ የውጪ ድርጅት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡
ሆለታ የሚገኘው የእንስሳት ኮቴ እንስሳት መከለያና ትምህርት ማዕከል በቦርን ፍሪ ፋውንዴሽን ኢትዮጵያ ከ15 አመታት በፊት የተቋቋመ ነው፡፡ እንስሳት ከተለያዩ ህገወጦች በመሰብሰብ በመንከባከብ ላይ የሚገኘው ቦርን ፍሪ ፋውንዴሽን ከኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር እየሰራ የሚገኝ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት መሆኑን አቶ በረከት ግርማ የማዕከሉ ስራስኪያጅ ገልጸዋል፡፡
