ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፎሎውሺፕ ኢትዮጵያ (justice for all prison fellowship Ethiopia) እና ኢንፓወር ኔክስት ጀነሬሽን ኢትዮጵያ (empower next generation Ethiopia) ከተባሉ ሀገር በቀል ድርጅቶች ጋር በመሆን ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናል ውይይት ተክብሮ ውሏል፡፡
ዓለም ዓቀፉ የወጣቶች ቀን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በየዓመቱ ነሀሴ 12 የሚከበር ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለሁለት ቀናት በአረንጓዴ ክህሎት (green skill) እና በዴሞክራሲ ባህል ወጣቶችን መገንባትና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የተረጋጋ ወደፊትን መገንባት (Empowering youth & engaging stakeholders; building a sustainable future through democratic culture and green skill) በሚል መሪ ቃል በአዲሱ የጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፎሎውሺፕ ኢትዮጵያ (justice for all prison fellowship Ethiopia) የልህቀት ማዕከል ተከብሯል፡፡
በመርኃ ግብሩ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱን ጨምሮ የጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፎሎውሺፕ ኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ገዛኸኝ እንዲሁም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወጣት ሰራተኞችና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የፓናል ውይይቱ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የተካሄደ ሲሆን በመርኃ ግብሩ ላይ የአረንጓዴ ክህሎትን መነሻ በማድረግ አረንጓዴ አሻራን የማስቀመጥ መርኃ ግብር ተከናውኗል፡፡