የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ አዲስ ተሹመው ወደ ተቋሙ ከመጡት አቶ ሳምሶን ቢራቱ ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡

ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የትውውቅ እና የስራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ለማስቀጠል በቁርጠኝነት ከአመራሩ እና ከአጠቃላይ ሰራተኛው ጋር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው በቆይታቸው ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እንዲሁም በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅችና በባለስልጣን መስሪያቤቱ መርህን መሰረት ያደረገ የስራ ግንኙነት እንዲኖር ተችሏል ያሉ ሲሆን ይህ የመጣው ውጤት የሁሉም ሰራተኛና አመራር ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በዚህ ተቋም እና ዘርፍ በማገልገሌ ደስታ ይሰማኛል በማለት አዲስ ተሹመው ወደ ተቋሙ ለመጡት ሃላፊ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡