• ግብዐቶች
  • ኩነቶች
  • ዓመታዊ ሪፖርቶች
  • መልቲሚዲያ
  • Call For Paper
  • ማስታወቂያዎች
  • አግኙን
  • English
ACSO
  • ሲ.ማ.ድ
    • ለአዲስ የሲ.ማ.ድ
      • አዲስ ሲ.ማ.ድ ማስመዝገብያ መስፈርቶች
    • የተመዘገቡ የሲ.ማ.ድ
      • ሀገር በቀል
      • የውጪ ሀገር
      • የሙያ ማኅበራት
      • የብዙሃን ማህበር
      • የበጎ አድራጎት ኮሚቴ
      • ቦርድ መር
      • በክልል የተመዘገቡ
    • ስለ ሲ.ማ.ድ.ባ የምርመራ ስልጣን
      • ባለስልጣኑ ምን ሊመረምር ይችላል
      • ባለስልጣኑ መመርመር የማይችላቸው ጉዳዮች
    • ሲ.ማ.ድ ስለመቆጣጠር
      • ሲ.ማ.ድ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች
      • ሲ.ማ.ድን ስለመቆጣጠሪያ
      • የቅሬታ/የስጋት ምክንያቶች/አይነቶች
  • ስለ ባለስልጣኑ
    • መረጃ
      • ስለ ባለስልጣኑ
      • የባለስልጣኑ ስልጣንና ተግባራት
      • የተቋም አደረጃጀት
      • ሕጎች
      • አጋሮች
    • የስራ ክፍሎች
      • ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቢሮዎች
      • መሪ ስራ አስፈፃሚ
      • ስራ አስፈፃሚ
    • ለማህበረሰብ
      • መግለጫዎች
      • ክፍት የስራ እድሎች
  • ዜና
  • የበጎ ፈቃደኞች መመዝገቢያ
    • ለበጎ ፈቃደኞች
    • ለአጋር ድርጅቶች
    • ለበጎፈቃደኛ አስተባባሪዎች
  • ቅሬታ ማስተናግጃ
  • ኢ-ሰርቪስ
  • ግብዐቶች
  • ኩነቶች
  • ዓመታዊ ሪፖርቶች
  • መልቲሚዲያ
  • Call For Paper
  • ማስታወቂያዎች
  • አግኙን
  • English

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለሁለተኛ ዙር በጫንጮ ከተማ ጎርፎ ቀበሌ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂዷል ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለሁለተኛ ዙር በጫንጮ ከተማ ጎርፎ ቀበሌ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም አካሂዷል ፡፡

ተቋማችን ከህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን የታላቁን ህዳሴ ግድብ ከደለል ስጋት ለመታደግ ‹‹አሻራችንን ለታላቁ ህዳሴ ግድባችን›› በሚል መሪ ቃል ዛሬ በጫንጮ ከተማ ጎርፎ ቀበሌ ከተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በጋራ ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሃግብሩ ላይ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንደተናገሩት ተቋማችን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር በቅርቡ የህዳሴ ግድብ በሚገነባበት ጉባ በመገኘት ግድባችን ያለበትን ሁኔታ ተመልክተናል አፈፃፀሙም ኩራት ፈጥሮብናል፤ ፀሃይና ሃሩር ሳይበግራችው ሌት ተቀን ግድቡን እየሰሩ ላሉ ባለውለታዎቻችንም ክብር ሰጥተን ተመልሰናል ብለዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ህዝብና አገርን በሚጠቅሙ ችግኞችን የመትከል እንዲሁም ታላቁ የህዳሴ ግድባችን በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ሃይል በማመንጨት ለአገራችን ብርሃንን እንዲሰጥ ለሚያደርጉት ያላሳለሰ ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
እንደሃገር በአንድ ጀምበር በመላው ህዝባችን ርብርብ የተሰበረውን ሪከርድ አስታውሰው ከተባበርን እና በጋራ ከተንቀሳቀስን የጋራ የሆነ ደማቅ ድል ማስመዝገብ እንችላለን ይህንንም አፈፃፀማችን አረጋግጦልናል ሲሉ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡ በዛሬው እለት ሁላችንም በርካታ ችግኞችን በመትከል የየግላችንን ሪከርድ እንድንሰብር እና የተሻለች ኢትዮጵያን በመገንባቱ ሂደት ላይ ታሪካችንን እንድንከትብ አደራዮን እያቀረብኩ ለምታደርጉት አስተዋፅኦ ሁሉ ምስጋዮን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የዛሬውን ታላቅ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በጋራ ላዘጋጀውና ላስተባበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች፣ ለጫንጮና አከባቢው አስተዳደር አመራሮችና ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የካ ተራራ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክርቤት በየካ ተራራ የ2015 ዓ.ም 500 ሚሊዮን የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ‹ነገን ዛሬ እንትከል›› በሚል መርሃ ግብር የተቋማቱ አጠቃላይ ሰራተኞች ከፍትህ እና ተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን በየካ ተራራ ላይ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

2ተኛው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተቋማዊ የንባብ ቀን በድምቀት ተካሄደ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች ተሳታፊ የሆኑበት ተቋማዊ የንባብ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ በፍቃዱ ወልደሰንበትን ጨምሮ በርካታ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
መርኃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በፍቃዱ ወልደሰንበት እንዳሉት ተቋማዊ የንባብ ሳምንቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ሰራተኞች የንባብ ባህል እንዲጎለብት ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያደርግ መርኃ ግብር መሆኑን ገልጸው ከተለያዩ የተቋሙ ሰራተኞች የህይወት ልምድ የሚቀሰምበትና እርስ በርስ የሚያቀራርብ መድረክ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በመርኃ ግብሩ ላይ የተለያዩ የስነጽሁፍ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን የተቋሙ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ በፍቃዱ ወልደሰንበትና የሰው ኃብት የብቃትና የልማት ቡድን መሪ አቶ መስፍን ማጎ የንባብ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

በተጨማሪ

November 3, 2026

የኢፌደሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ አከበረ፡፡

November 3, 2026

የEthiopian Intergenerational dialogue initiative ማስጀመሪያ መድረክ ተካሄደ፡፡

November 3, 2026

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ሴቶች ፎረም ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ።

ወደ ዜና ገጽ
ስለ ባለስልጣኑ

ሲ.ማ.ድ.ባ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ለመመዝገብ ፣ ለመደገፍ እና ለመከታተል የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነው ፡፡

ይፈልጉ
  • እንዴት ማመልከት ይቻላል
  • አገልግሎቶች
  • ይጠይቁን

””

  • Today's visitors:206
  • Today's page views 317
  • Total visitors 93,118
  • Total page views 157,916
አድራሻ

ቸርችል ጎዳና ፣ ቴዎድሮስ አደባባይ ፣ ህብረት ኢንሹራንስ ህንጻ ከ4-8 ፎቅ ፣ አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ

ለመነጋገር

ኢሜል:  info@acso.gov.et

ስልክ: +251 115 582378
ስልክ 2: +251 115 582379
ፋክስ: (011) 558 1825
የፖስታ ሣጥን: 14340

© 2026 ACSO. All rights reserved

Privacy Preference Center

Privacy Preferences

Skip to content
Open toolbar Accessibility Tools

Accessibility Tools

  • Increase TextIncrease Text
  • Decrease TextDecrease Text
  • GrayscaleGrayscale
  • High ContrastHigh Contrast
  • Negative ContrastNegative Contrast
  • Light BackgroundLight Background
  • Links UnderlineLinks Underline
  • Readable FontReadable Font
  • Reset Reset