ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ጋር በጋራ ለመስራት መከረ፡፡
ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በሚኒስትሮች ደንብ ቁጥር 552/2015 መሰረት የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ተልዕኮ ያለው መንግስታዊ ተቋም ሲሆን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ጋራ በቅንጅት የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተወካይ አቶ ተስፋዬ ሽፈራው የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ እንዳሉት የመደራጀት መብትን የሚያከብር ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባ ወሳኝ የሆነና የሲቪል ማህበራት በአገር ዕድገት ውስጥ ያላቸው ሚና ለማጎልበት የሚያስችል ህግ ወጥቶ ተግባራዊ ከሆነ ወዲህ በዘርፉ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል፡፡

አያይዘው በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶች መድረሳቸውን አንስተው ለአራት ተከታታይ ዙር የሲቪል ማህበረሰብ ደርጀቶች በገንዘብና በዓይነት ድጋፍ ማድረጋቸውን አንስተዋል፡፡ ሌላው ያነሱት የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገው ጥረት የሁሉም ዜጋ ተሳትፎና ድጋፍ የሚጠይቅ በመሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች እንደዚህ ቀደሙ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላለፈዋል፡፡ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ባስተላለፉት መልዕክት አገራች ኢትዮጵያ ላለፉት ወቅቶች ችግሮች ውስጥ እንደነበረች አንስተው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ሰላም ከወረደ በኋላ በጣም ውስብስብ ከሆኑ ጉዳዮች አንድ የቀድሞ ተዋጊዎች መልሶ ለማቋቋም እና ከህብረተሰቡ ጋር የመቀላቀል ስራ ብቻ ሳይሆን ከጦርነት ወጥተው ለአገረ ሰላም፣ ልማት ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አስተዋጽኦ የሚደርጉ ዜጎች እዲሆኑ ለማስቻል ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አምባሳደሩ አክለውም የተጀመሩ ስራዎችን ቀጣይነት እንዲኖረው እና ግቡን እንዲመታ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ የምክክር መድረኮች በማዘጋጀት ውይይቶች መደረጋቸውን አንስተው የሲቪል ማህበረሰብ ደርጀቶችም ከዚህ ረገድ ግንዛቤ እንዲይዙ እና በቀጣይ እንዴት አብሮ መስራት ስለሚያስችሉ ጉዳዬች ለመወያየት መድረኩ መፈጠሩን አንስተዋል፡፡


