ሁለተኛው የኤዢያ አፍሪካ ወጣቶች ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል ፡:

ሁለተኛው የኤዢያ አፍሪካ ወጣቶች ፎረም ላይ ከተለያዩ አፍሪካ እና ኤዢያ ሀገራት የተገኙ ከሶስት መቶ በላይ ወጣቶች በአዲስ አበባ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ ፡፡
ዝግጅቱ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ኦ የስ ግሎባል ፋውንዴሽን (O-YES GLOBAL FOUNDATION) ነው ፡፡
የ ኦ የስ ግሎባል ፋውንዴሽን (O-YES GLOBAL FOUNDATION) ዋና ዳይሬክተር አቶ ከማል አብደላ እንደተናገሩት የዚህ ፎረም ዋና ዓላማ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ወጣቶች የተለያዩ ልምድ የሚለዋወጡበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረው በዚህም የኤዢያ አፍሪካ ወጣቶች ፎረም ውይይት ወጣቶች ፍላጎቶቻቸው፣ ተግዳሮቶቻቸው፣ጉልበታቸውን፣የፈጠራ ሃሳቦቻቸውን፣የቴክኖሎጂ ትስስር በመጠቀም ለተሻለ የአፍሪካ-እስያ አጋርነት ሁለንተናዊ ለውጥ በማምጣትና በማበርከት የማይተካ ሚናቸውን የሚጫወቱበት ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
አክለውም አቶ ከማል ወጣቶቹ በፎረሙ በጤና፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የወጣቶች ኢኮኖሚ ማጎልበት፣ ሰላም እና አቅም ግንባታ እንዲሁም በጎ ፈቃደኝነት ላይ ተሞክሯቸውን ይለዋወጣሉ ብለዋል።
በፎረሙ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደተናገሩት በጎ ፈቃደኝነት ለወጣቶች የግል ልማት እና የዕድገት ብሎም የቡድን ሥራን በማሳደግ መልካም ስነምግባርን ያበረታታል በማለት የመንግስት/መንግስታዊ ያልሆኑ ተዋናዮች ከዚህ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው በመድረኩ ተናግረዋል ።
አክለውም በጎ ፈቃደኞች እና ተጠቃሚዎች በህብረተሰቡ ውስጥ ወሳኝ-ገንቢ ሚና ይጫወታሉ ያሉ ሲሆን እነዚህም በጋራ በመሆን ለዘላቂ ልማት፣ ማህበራዊ ትስስር እና መረጋጋት ትልቅ አስተዋፅዖ ይኖራቸዋል ብለዋል ፡፡
ይህም አፍሪካ እና እስያ ወጣቶች ፎረም ወጣቶች በየጊዜው ለሚለዋወጧቸው ፍላጎቶች፣ ተግዳሮቶቻቸው እና ምኞቶቻቸው ምላሽ የሚሰጡ አዳዲስ አቀራረቦችን ያመነጫሉ፣ ጉልበታቸውን፣ የፈጠራ ሃሳቦቻቸውን፣ ቴክኖሎጂዎችን፣ እና የእርስ በርስ ትስስርን እንዲኖራቸው የሚያስችል ሲሆን ይህምበ የሚያበረታታና ለSDGs ስኬት አስተዋፅዖ በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
በመጨረሻም በ2ኛው የአፍሪካ እስያ የወጣቶች መድረክ (AAYF 2023) አዘጋጆች (O-YES Global Foundation) ልዩ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ ገልጸዋል ፡፡