በምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ የሚመራ ልዑካን ቡድን በባንግላዴሽ ሃገር የልምድ ልውውጥ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

በCSSP2 ድጋፍ የተዘጋጀው የልምድ ልውውጥ ላይ ከተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተር በተጨማሪ ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ዘርፉን የሚመሩ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡:
ልዑካን ቡድኑ ባንግላዴሽ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን የሚመዘግብና የሚቆጣጠር ተቋማት ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚያከናውኗቸውን ተግባራት ተመልክተዋል፡፡
በልምድ ልውውጡ ወቅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በ ኢትዮጵያ ከ2018 ጀምሮ በዘርፋ በርካታ የህግና የአሰራር ሪፎርም መደረጉን እና በዘርፉም ከዚህ ረገድ ለውጦች እየተመዘገቡ መምጣታቸውን አስረድተዋል፡፡
አሁን ያለውን ለውጥ ለማስቀጠልና ዘርፉን የበለጠ ለማሳደግ የሌሎች ሃገራት ተሞክሮን ለመውሰድ የክልል አስፈጻሚ አካላትን ያካተተ የልምድ ልውውጥ በባንግላዴሽ ሃገር ማድረግ ማስፈለጉን አያይዘው ገልጸዋል፡፡