ሚዲያና ኮሙኒኬሽን የጋራ መግባባትን ለማምጣት ትልቁ መሳሪያ ነው ሲሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ገለጹ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮቹ በተግባቦትና ተቋማዊ ውጤታማነት (communication and organizational effectiveness) እንዲሁም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን አሁናዊ ሁኔታ የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን እንደተቋም ምን ፋይዳ እንዳለው እንዲሁም ተቋማዊ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ፖሊሲ ለማዘጋጀት ግብዓት ለማሰባሰብ ነው፡፡
በመርኃ ግብሩ መክፈቻ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንዳሉት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን የጋራ መግባባትን ለማምጣት ትልቁ መሳሪያ መሆኑን አንስተው በዚህ ረገድ እንደተቋም ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
ወደማህበረሰቡ መረጃን አደራጅተን መላክ የምንችለው በኮሙኒኬሽን ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የተቋሙን ራዕይ፣ እሴት እና ተልዕኮ መሰረት በማድረግ ስለተቋማችን የተሻለ ምስል መፍጠር መቻል አለብን ብለዋል፡፡ አክለውም ስለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተሳሳተ አረዳድ ያላቸው አካላትንም መረጃ ለመስጠት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን በአግባቡ መጠቀም አለብን ብለዋል፡፡
በ Communication and organizational effectiveness ዙሪያ አቶ ነጻነት ሃይሉ የህዝብ ግንኙነት፣ሚዲያና ኮሙኒኬሽን አማካሪ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የባለስልጣን መስሪያቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ትዕግስት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተሰሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራዎች እና የሚታዩ ክፍተቶች ፣ የመደመር ትርክት፣የቀውስ ግዜ እቅድ እና አጀንዳ ሴቲንግ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
አክለውም በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ አስፈላጊነት እንዲሁም የቀውስ ጊዜ እቅድ በመንደፍ መምራትና ተቋሙ የመንግስት ተቋም እንደመሆኑ መጠን በዚሁ ማዕቀፍ ውስጥ መንቀሳቀስ ስለሚችልበት ሁኔታዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡