የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሴቶች የመረብ ኳስ ቡድን የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነ፡፡

በ16ኛው የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የተሳተፈው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የስፖርት ልዑክ ባደረገው የመጀመሪያ ተሳትፎ በሴቶች መረብ ኳስ የብር ሜዳሊያ በማሸነፍ አጠናቋል፡፡ በጥሩ መነሳሳት ውድድሩን የጀመሩት የባለስጣን መስሪያ ቤቱ የሴቶች መረብ ኳስ ቡድን የምድብና የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎችን በስኬት አጠናቆ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የፍጻሜ ጨዋታውን አድርጓል፡፡
ቡድኑ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በድምሩ ሁለት ለአንድ (2፡1) በሆነ ውጤት በኢትዮ ቴሌኮም አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮም የዋንጫ አሸናፊ ሲሆን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል፡፡ 16ኛው የፌዴራል መስሪያ ቤቶች ስፖርታዊ ዉድድር ማጠቃለያውን  ሚያዚያ 17/2015 ዓ.ም በተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚያደርግ ይሆናል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የሴቶች መረብ ኳስ ቡድን ላስመዘገበው ውጤት ከፍተኛ ደስታ የተሰማው መሆኑን ይገልጻል፡፡