የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን CERFODES ከተባለው ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት ጋር የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ ፡፡

የባለስልጣን መስርያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ፣ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከአማካሪው ድርጅት የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል ፡፡ ቀደም ሲል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከፈረንሳይ መንግስት የልማት ድርጅት (AFD) ጋር በመተባበር (To Strengthen the Institutional Capacity of ACSO) የሚል ፕሮጀክት በመቅረጽ የውጭ አማካሪ ድርጅቶችን የማወዳደር ስራ የተከናወነ ሲሆን በዚሁ መሰረት (CERFODES) ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡ ከአሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም የተቋሙን አቅም ለመገንባት ፣ ለማዘመን እና በቀጣይ በጋራ መከናወን ስለሚገባቸው ጉዳዬች ውይይት በማድረግ የስራውን ማስጀመርያ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡