የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በዱብቲ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት ኤም ኤስ ኤፍ ቤልጄም እና አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ በእናቶችና ህጻናት ጤና እንዲሁም ተላላፊ ባልሆኑና ቲቢን መሰረት አድርገው እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በተጨማሪ የክልሉ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ደረሳ መሀመድ እና የዱብቲ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅን ጨምሮ የሁለቱም ድርጅቶች ኃላፊዎችና ፕሮጅክት አስተባባሪዎች በጉብኝቱ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ኤም ኤስ ኤፍ ቤልጄም(MSF Belgium) እና አምረፍ ኸልዝ አፍሪካ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሲሆን በአፋር ክልል ዱብቲ አጠቃላይ ሆስፒታል ኤምኤስኤፍ ቤልጀም ከ120 በላይ ሰራተኞችን በመያዝ በወባና ተያያዥ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች እንዲሁም የቲቢ ተጠቂዎችን በመርዳት ላይ የሚገኙ ሲሆን አምረፍ ኸልዝ አፍሪካ (Amref health Africa) ደግሞ ለሆስፒታሉ የጤና መሰረተ ልማቶችን ከማሟላት ባለፈ የአንድ ማዕከል (one stop center) በማቋቋም; በሆስፒታሉ ውስጥ አገልግሎት ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡