የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚንቀሳቀሱና ለዞን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዴስክ ሃላፊዎች የሚሰጠው ስልጠና እንደቀጠለ ነው፡፡

ስልጠናው በአፋር ብሄራዊ ክልል የተካሄደ ሲሆን በዚህ ስልጠና ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንዲሁም የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ ዘርፍ ምክትል ሃላፊ እንዲሁም የዞን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዴስክ ሃላፊዎችና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ መመሪያዎቹ ሲዘጋጁ ጀምሮ ተግባር ላይ እስኪውሉ ድረስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተው ይሁንና ድርጅቶች የሚያከናውኗቸው የልማት ስራዎች መንግስት ከሚያወጣቸው የልማት ፖሊሲዎችና እቅዶች ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን የመከታተልና የማረጋገጥ ኃላፊነት የፌደራልና የክልል የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ነው ብለዋል፡፡
ዘርፉ በፍጥነት እያደገ የመጣ ዘርፍ መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ አስፈጻሚ አካላት ስለዘርፉ እድገትና የእንቅስቃሴ ሁኔታ በመገምገም የህዝቡን የላቀ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡበትን ስርዓት መዘርጋት ይኖርባቸዋል ያሉ ሲሆን በህዝብ ስም የሚመጣ ማንኛውም ድጋፍ ለህዝብ ጥቅም ብቻ መዋሉን የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግስት ኃላፊነት እንደመሆኑ ይህንንም በኃላፊነት ስሜት መወጣት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አክለውም በመድረኩ የቀረቡት መመሪያዎች በህዝብ ስም የሚመጡ ሀብቶች ለህዝብ ጥቅም መዋላቸውን ማረገጋገጥ፤ ድርጅቶች ያላቸውን ሀብት በቁጠባና በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ ለማስቻል በውጪ ድጋፍ ላይ የተመሰረተው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የገቢ ምንጭ ዘርፈ ብዙ እንዲሆንና በተለይም ከሀገር ውስጥ ገቢ ማሰባሰብ እንዲችሉና በጎ ፈቃደኝነትን ለማበረታታት፤ ማህበረሰቡን ማነቃነቅ እና በራሳችን ጥረት ከገባንበት ችግሮች መውጣት የምንችልበትን መንገዶች እንዲቀይሱ የሚያስችሉ መመሪያዎች ናቸው ብለዋል፡፡

Change the color to match your brand or vision, add your logo, choose the perfect layout, modify menu settings, add animations, add shape dividers, increase engagement with call to action and more.

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የኢኮኖሚክ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረሳ መሀመድ በበኩላቸው ዝቅተኛ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ቁጥር ካሉባቸው ክልሎች አንዱ የአፋር ብሄራዊ ክልል እንደሆነ አንስተው ከፍተኛ የልማት ፍላጎት፣የተጎጂ ማህበረሰብ ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት ብቻ የሚያደርገው ጥረት በቂ አይደለም ያሉ ሲሆን ከአጋር አካላት ጋር በትብብር መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ አክለውም ክልሉ ፋታ በማይሰጥ ከፍተኛ ግጭት ውስጥ እንደነበር ገልጸው ይህን የሚፈታ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ለህብረተሰባችን ለመድረስ እነዚህ መመሪያዎች እንደሚያግዙ የተናገሩ ሲሆን ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮም ድርጅቶች የሚገጥማቸውን ችግሮች ለመቅረፍ መመሪያዎቹ ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው አንስተዋል፡፡ በጸደቁ መመሪያዎች ላይ የሚሰጠው ስልጠና በተለያዩ ክልሎች የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም በሲዳማ እና በደቡብ ምዕራብ ክልሎች የሚካሄድ ይሆናል፡፡

Change the color to match your brand or vision, add your logo, choose the perfect layout, modify menu settings, add animations, add shape dividers, increase engagement with call to action and more.