በመድረኩ የፌደራል ባለድርሻ አካላት፣የተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ተወካዬች እና የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለምአንተ አግደው እንደገለጹት መንግስት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑ በማንሳት ለትርፍ ያልተቋቋሙና ለፖለቲካ ያልወገኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአገራዊ የልማት እንቅስቃሴ እና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አይነተኛ ሚና ያላቸው መሆኑ ስለሚታመን ላለፉት ዓመታት የህግ እና ተቋማዊ ሪፎርም ሲካሄድ ቆይቷል ብለዋል፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ አቅም እየገነቡ እና መልካም አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን በሚያደርጓቸው እንቅስቀሴዎች መገንዘብ ይቻላል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ሲማዶች በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ በጦርነትና ድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች በገንዘብ በዐይነት እያደረጉ ያሉት ድጋፍ አንድ ለህዝብ ተጠቃሚነት ከቆመ ዘርፍ የሚጠበቅና ምስጋና የሚቸረው ጉዳይ ነው ሆኖም ሲማዶች በወቅታዊ ጉዳይም ሆነ ሀብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ እያደረጓቸው ያሉት አስተዋፅኦዎች መንግስት ከፈጠረው ምቹ ሁኔታ እና ከአገርና ህዝብ ፍላጎት አንጻር ሲታይ አሁንም ብዙ የሚቀረው እና መሻሻል የሚጠበቅበት ነው ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደገለጹ በባለፉት ስድስት ወራት የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ በኢ-ሰርቪሲ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን፤ አገልግሎት አሰጣጥ የጥራት ደረጃ በአማካይ 87.71% መድረሱ፣ 326 አዲስ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተመዝግበው የምዝገባ ሰርተፍኬት እንዲያገኙ መደረጉ፣ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የክትትልና ግምገማ ስርዓታችንን በማጠናከር የ1,047 የዴስክ ክትትል መደረጉ፣ በመስክ ለድርጅቶች ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ በተሰራው ስራ ከተያዘው እቅድ አንጻር 92.76% መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
ከእቅድ አንጻር የሲቪል ማኅበረሰብ ዘርፉን ሚናና ተሳትፎ በማሳደግ የበለፀገች አገር የመገንባት ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ዜጎች የልማቱ ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ፣ብቁ፣ገለልተኛና ነጻ የህዝብ አገልግሎት ሥርዓት በመገንባት የመንግስትን የመፈፀም ብቃት በማጎልበትና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የዜጎች እርካታ ማሳደግ እና ሠላምና ፍትሕን የሚያረጋግጡ ጠንካራ ሥርዓትን በመገንባትና የሕግ የበላይነትንና ሰብአዊ መብትን በማስከበር፣ የዜጎችን ደህንነት በማረጋገጥ ጉዞ ውስጥ የሲቪል ማኅበረሰቡ ዘርፍ ሚና ከመቸውም ጊዜ በላይ ጎልቶና ጎልብቶ እንዲታይ ተደርጎ የተዘጋጀ ዕቅድ ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡
Click the button