የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበረን በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ማህበር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች ማህበር ፕሬዝዳንት ኮሎኔል እስቲፋኖስ ገ/መስቀል ማህበሩ በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ጊዜ በኮሪያ ዘምተው የነበሩ ወታደሮች ለማስታወስና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ የተቋቋመ ማህበር መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የማህበሩን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ለዋና ዳይሬክተሩ ያብራሩ ሲሆን በዋናነት ማህበሩ ከኮሪያ መንግስት የሚያገኘው ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንዳሉት ይህ ማህበር የኢትዮጵያዊነት፣ የጀግንነት እና ለሌሎች መስዋት የከፈሉ ጀግኖች ያቀፈ እንዲሁም ኢትዮጵያን በአለም መድረክ ላይ እንድትታወቅ ስሟ እንዲጠራ ያደረጋችሁ ጀግኖቻችን ናቹ ሲሉ አሞካሽተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በጀግንነት ምሳሌ እንድትሆን ፣ ለብዙ አገራት መስዋት የሆነች ስሟ በአለም አደባባይ በጀግነንነት እንድትጠራ፣ የብዙ ታሪክ ባለቤት እንድትሆን ካደረረጉ ጀግኖች መካከል የኮሪያ ዘማቾች ተጠቃሽ ናቸው በማለት በናንተ መካከል በመገኘቴ ታላቅ ኩራትና ክብር ይሰማኛል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ሌላው ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ አገራችን በጦርነት ያሳየችውን ጀግንነት በልማት ለመድገም ተግታ እየሰራች መሆኑን አንስተዋል፡፡
የደቡብ ኮሪያ መንግስት ውለታን የማይረሳ መንግስት ነው የዛሬ 70 ዓመት ኢትዮጵያ ጀግኖች የከፈሉላትን ውለታ በማስታወስ አሁን አድገናል ብለው ለመደገፍ በማሰባቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለማህበሩ የሚችለውን ነገር ሁሉ ያደርጋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በዋናነት እናንተ ጀግኖቻችን፣ እናንተ የነጻነት ቀንዲሎች፣ የኩራታችን ምንጮች፣ በናንተ ውስጥ የማሸነፍ ምሳሌን ያየን በናንተ ጀግንነት ውስጥ ኢትጵያን እናያለን፣ ተስፋን እናያለን፣ ኢትዮጵያ የነጻነት ምልክት ሆና እንደቆየችው በልማትና በዴሞክሲያዊ ስርዓት ግንባታ ወደፊት እንደምትመጣ አንጠራጠርም ሲሉ ገልፀዋል፡፡