የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተቀላጠፈ የአገልግሎት አሰጣጥ ለመዘርጋትና በአዋጅ የተሰጠውን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ለተቋሙ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ በስልጠናው ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንዳሉት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአስር አመት ስትራቴጂ እቅድ በማዘጋጀት ወደስራ መግባቱን ገልፀው በእቅዱ ውስጥ አምስት ግቦች የተቀመጡ ሲሆን እነሱም ምቹ የፖሊሲና የቁጥጥር ስርዓት፣ የበጎ ፈቃድና የበጎ አድራጊነት ባህልን ማዳባር፣ የአገልግሎት ተደራሽነት ስርዓት፣ በየዘርፉ ያሉ ተቋማት ጋር አጋርነት መፍጠር እና የባለስልጣን መስሪያቤቱ ውስጣዊ አቅም ማጎልበት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የህዝባችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የዳበረ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመፍጠር በእውቀትና በስነምግባር የታነፀ እንዲሁም ማገልገል ክብር መሆኑን የሚያውቅ ባለሙያ ሲኮን መሆኑን አንስተዋል፡: ሌላው ያነሱት በአራት ዓመታት ውስጥ ተቋማችንን የተሻለ የስራ አፈጻጸም እንዲኖረው ለሰራተኛው የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መሰጠቱን አስታውሰው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጎን በመሆን ስልጠናዎችን በመስጠት ድጋፍ ያደረገ ያለውን CCP2 አመስግነዋል፡፡ ስልጠናው team building, communication organization effectives እና safeguard ያተኮረ ነው፡፡