THE NATURE AND BIODIVERSITY CONSERVATION UNION /NABU/ ሪጅናል ቢሮውን መክፈት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ነው ከባለስልጣን መስሪያቤቱ ጋር የተፈራረመው፡፡ ድርጅቱ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ላይ ተሰማርቶ የሚሰራ ሲሆን ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እና የተፈጥሮ ሃብትም ያለአግባብ እንዳይወድም ተገቢውን እንክብካቤ የሚያደርግ ድርጅት መሆኑን ተገልጷል፡ የመግባቢያ ሰነድ ዋና ዓላማ በአፍሪካ ሪጂናል ቢሮ እንዲኖረው ለማስቻል ብሎም ከሌሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በቅርበት ለመስራት እንዲያስችል መሆኑን በአፍሪካ ሪጅናል ኦፊስ አክቲንግ ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ አስፋው ተናግረዋል፡፡