በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ጳጉሜ 04/2014 በመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር የተገኙት የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እና የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በቆይታቸው በመቄዶኒያ ድጋፍ እተደረገላቸው ያሉ አረጋውያንና የአእምሮ ህሙማንን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በተጨማሪም ድርጅቱ የሚሰጠውን አገልግሎት ዘላቂነት ለማረጋገጥ እያስገነባ ያለው ግዙፍ ህንፃ የተጎበኘ ሲሆን ህንፃው በሶስት ዓመት ከግማሽ ጊዜ ውስጥ 70 ፐርሰንት በላይ መድረሱ የሚያስመስግን መሆኑ ተገልፆል፡፡ የድርጅቱ መስራችና ስራ-አስኪያጅ የሆኑት የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ የእንክብካቤ ማእከሉን አስጎብኝተዋል፡፡ ከማእከሉ ከሚገኙ አረጋውያን ጋርም ዋዜማውን በማስመለከት ፕሮግራም የተደረገ ሲሆን ድርጅቱ የሚያደርጋቸውን ስራዎች የሚያሳይ ዶክመንታሪ ቀርቧል፤ አረጋውያኑ የአዲስ ዓመት ዋዜማን አብራችሁን ስላከበራችሁ እጅግ ተደስተናል በማለት የገለፁ ሲሆን ምስጋናቸውን በአባታዊና እናታዊ ምርቃት ገልፀዋል፡፡

May be an image of 5 people, people standing and indoorMay be an image of 1 person, standing and indoorMay be an image of outdoors

ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን መቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር እያከናዎነ ያለው ስራ አስደናቂ መሆኑን በመግለፅ የማህበሩ እንቅስቃሴ እንደአገር ልንማራቸው የሚገቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ስራ የማከናዎን፣ የአብሮነት፣ የወንድማማችነት፣ የአንድነትና የመረዳዳት እሴቶችን በስፋት ማዳበሩን መረዳት መቻላቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ኢትዮጵያ እንደመቄዶኒያ መሆን ያለበት መሆኑን አስመረው ተናግረዋል፡፡ አዲሱ ዓመት መቄዶኒያ የበለጠ አገልግሎቱን የሚያስፋበትና ስኬታማ የሚሆንበት እንዲሆን በመመኘት እና ለተቋሙን አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እንደሚያደርጉ በመግለፅ ለመላው የመቄዶኒያ ማህበረሰብ በሙሉ መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡ የባለስልጣኑ አመራሮች ለመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ስራ-አስኪያጅ እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቹ እያከናዎኑ ላሉት ለትውልድ ተሻጋሪ ለሆነው መልካም ስራ ከፍተኛ ምስጋናቸውን በማቅረብ ማህበሩ እንዲጠናከር አስፈላጊውን የቅርብ ድጋፍ የሚያደርጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ መቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር ከ7500 በላይ ጧሪ ደጋፊ የሌላቸውን በጎዳና ላይ ይገኙ የነበሩ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማንን አቅፎ እንክብካቤ የሚሰጥ ውጤታማ መልካም ተቋም መሆኑ በጎብኝቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡