የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለተቋሙ ሰራተኞችና ለመላው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም የአገልጋይነት ቀንን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የአገልጋይነት ቀን በልዩ ሁኔታ ሲከበር የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተገልጋዮች መረጃ በመስጠት እንዲሁም ለተቋሙ ሰራተኞችና ተገልጋዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትን የያዙ ካርዶችን በመስጠት እና በዛሬው እለት አገልሎት ፈልገው ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ለአዲስና ዳግም ምዝገባ ላደረጉ የተወሰኑ ድርጅቶች አገልግሎቱን ባሉበት በመሄድ እንኳን አደረሳችሁና የምዝገባ ሰርተፍኬት ሰጥተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ለየድርጅቶቹ የምዝገባ የምስክር ወረቀቱንና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ላለፉት 4 ዓመታት በርካታ የህግ ማሻሻያዎችን በማድረግና የተቋም ግንባታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸው በ2015 ዓ.ም እንደሁልጊዜው ሁሉ ፍጹም የአገልጋይነትን መንፈስ በመላበስ ተገልጋዮችን የበለጠ ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ድርጅቶቹ የምዝጋባ ሰርተፍኬቱን ከተቀበሉ በኋላ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እየሰጠ ስላለው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት አመስግነው ለሀገርና ለህዝብ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት በትጋት እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡
May be an image of 4 people, people standing and indoorMay be an image of 2 people, people sitting, people standing, suit and indoorMay be an image of 8 people and people standing