ባዛርና ኤግዚቪሽኑ ከጉብኝት እና ከመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ጎን ለጎን በአራት ርዕሰ ጉዳዬች ላይ የፓናል ውይይት ተደርጓል ፡፡ ውይይቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸው ሚና፣ከአዲሱ አዋጅ በኋላ የመጡ ለውጦች እንዲሁም ስርዓተ ጾታ እና ተያያዥ ጉዳዬች ተዳሰዋል፡፡ በመዝግያ መርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዓለምአንተ አግደው የተገኙ ሲሆን በንግግራቸውም ይህ ባዛርና ኤግዚቪሽን በመዘጋጀቱ ለዘርፉ እድገት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን እና ባዩት ስራ መደሰታቸውን ገልጸው ሚኒስትር መስሪያቤታቸው ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሚፈልጉት ድጋፍ ሁሉ ከጎናቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው የተሳካ ባዛርና ኤግዚቪሽን በመዘጋጀት ሂደት አስተዋጽኦ ላደረጉ ድርጅቶች ፣ተሳታፊዎችና አዘጋጅ ኮሚቴዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡