ድጋፉን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ እንደተናገሩት በተለያዩ ክልሎች ባጋጠመው ድርቅና በጦርነት ምክንያት ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ በማስተባበር ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ በገንዘብና በዓይነት መሰብሰብ መቻሉን እና ለአማራ፣ አፋር እና ዛሬ ደግሞ ለኦሮሚያ ክልል አስረክበናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሞ ህዝብና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስም የተሰጠውን ድጋፍ በማመስገን በህዝቡ ውስጥ የሚገኘውን የድጋፍ ባህልን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ብለዋል ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦችም እርስበዕርስ መደጋገፍ እንዳለባቸውም ተናግረዋል ፡፡ በመጨረሻም በክልሉ በጨፌ የፀደቀ በገዳ ስርዓት ባህል ቡሳ ጎኖፋ የተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የተቋቋመ መሆኑን በመግለፅ ይህም ተቋም የሰው ልጆችን ችግር ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡