የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከተለያዩ የሙያ ማህበራት ለተውጣጡ የሙያ ማህበራት ተወካዮችና ኃላፊዎች በቅርቡ ፀድቀው ስራ ላይ ከዋሉት 4 መመሪያዎች አንዱ በሆነው “የሙያ ማህበራት ድጋፍና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 849 ላይ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናው በዋናነት የሙያ ማህበራት ድጋፍና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 849 ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን የሙያ ማህበራትን በተመለከተ ስለሚደረጉ ድጋፎች፣ የሙያ ማህበራት የምዝገባ ስርዓት፣ የሙያ ማህበራት ተግባራትና ሊሰማሩባቸው የሚችሉ የስራ ዘርፎች፣ በሙያ ማህበርነት መመዝገብ ስለማይችሉ ማህበራት በተመለከተ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል፡፡b ከተሳታፊዎች የሙያ ማህበራት ለሶስተኛ ወገን ስለመስራት፣ የተለያዩ ሀገራት ልምዶች ወደ ሀገር ውስጥ ስለሚገቡበት ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች ጥያቄዎችን አንስተው ዋና ዳይሬክተሩ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውበታል፡፡
በተጨማሪም “የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አሁናዊ ሁኔታ (the current status of professional associations in Ethiopia” በሚል ርዕስ በኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነት አሶሲየሽን (ERSA) መስራችና ፕሬዝዳንት አቶ ዮናስ ወልደሰማያት ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ስልጠናው በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፎረም ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡