በስልጠናው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስነምግባርና ጸረ- መስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትግስት አቡዬ እንደገለጹት የዚህ ስልጠና ዓላማ ሰራተኞች በግል ህይወታቸው እና በተሰማሩበት የሙያ መስክ የስነ-ምግባር እሴቶችን በመተግበር ከብልሹ አሰራርና ሙስና ነጻ የሆነ ሙያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በተያያዘም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ጌታቸው እንዳሉት የተቋሙ ሰራተኞች ብቁና ውጤታማ አንዲሆኑ እንዲሁም የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል ስልጠናዎች አጋዥ መሆናቸውን አንስተው በቀጣይም የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ከመስጠት ረገድ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ይህ ስልጠና ለሁለተኛ ዙር የተዘጋጀ ሲሆን ሰራተኞች ከስልጠናው በኋላ በስራ አካባቢያቸው መብትና ግዴታቸውን አውቀው መልካም ስነምግባርን ተላብሰው ለተቋሙ ውጤታማነት ቀደም ሲል ያደርጉ ከነበረው በተሻለ መልኩ እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል፡፡