ከዚህ ረገድ ነህምያ የኦቲዝም ማዕከል እና በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶችን አመስግነው ሌላው የማህበረሰብ ክፍልና ድርጅቶችም ኦቲዝም ላለባቸው ህጻናት ትኩረት ከመስጠት ረገድ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በነህምያ የኦቲዝም ማዕከል አዘጋጅነት የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ የእግር ጉዞ እና ሃይኪንግ ፕሮግራም መጋቢት 25/ 2014 ከ አዲሱ ገበያ አደባባይ እስከ ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የእግር ጉዞ እንዲሁም በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ተራራ የመውጣት ፐሮግራም መካሄዱን ይታወቃል፡፡ ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የተመዘገበ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ሲሆን ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ህፃናትን ማስተማር ማሰልጠን እና ከችግሩ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የክህሎት ድክመቶችን ለውጥ እንዲያመጡ እና አራሳቸውነወ የሚችሉ ብቁ ዜጋ ማድረግን ዓላማ ያደረገ ነው።