የኢንዱስትሪ ፓርኩ ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩ ወልዴ በገለጻቸው የስራ እድል ፈጠራ፣የቴክኖሎጂ ሽግግር፣የውጭ ምንዛሬ እና ግብርናን ማዘመን የኢንደስትሪ ፓርኩ አራት መሰረታዊ ጥቅሞች እንደሆኑ ለጎብኚዎች አስረድተዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ በበኩላቸው የሲዳማ ብ/ክ/መንግስትን እንደዚህ አይነት የጉብኝት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ተሳታፊዎቹ የልማት ስራዎችን እንዲመለከቱ በማድረጋቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ጎብኚዎቹም ባዩት ነገር እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡