ውይይቱ በዋናነት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ የመንግስት ሰራተኛው ሚና ምንድን ነው የሚል ሲሆን በዚህ ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ከውይይቱ በኋላ የባለስልጣን መስሪያቤቱ አመራርና ሰራተኞች 9 የአቋም መግለጫዎችን አውጥተዋል፡፡

  1. አሸባሪው ትህነግ/ህውሃት በአገራችን ህዘብ ትግል የተረጋገጠውን ለውጥ እንዲቀለበስ ከለውጡ መባቻ ጀምሮ ሳያሳልስ ሰው ሲገድል፣ ሲያፈናቅል አገራችን እንደትበታተን ሲሰራ የነበረውን እኩይ ተግባር ቀጥሎበት የአገር መከታ የሆነውን መከላከያችን በተለይም በሰሜን እዝ ላይ ያደረሰውን ጥቃት በፅኑ እናወግዛለን፤
  2. አሸባሪው ትህነግ/ህውሃት በአገራችን ላይ የጀመረውን ጥቃት አጠናክሮ በመቀጠል በአማራና አፋር ክልል እያደረገ ያለውን ወራር እንዲሁም እያደረሰ ያለውን ውድመት በከፍተኛ ደረጃ እናወግዛለን፤ ይህ ወረራ እንዲቀለብስ በአስፈላጊው ሁሉ እንፋለማለን፤
  3. በባለስልጣኑ መስሪያ ቤት ተመዝግበው በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የአገር በቀል እና የውጭ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የአገራችንን ህልውና የማስጠበቅ እንቅስቃሴው ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን፤ ህግን የሚተላለፉት ላይ ደግሞ ተገቢውን የእርምት እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  4. ምእራብውያን እና አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከአሸባሪው ጎን በመቆም አገር በማፍረስ ሂደት ላይ በመሳተፍ በአሳፋሪ የታሪክ መስመር ላይ እንዳይሰለፉ አካሄዳቸው ቆም ብለው እንዲመረምሩ እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፤
  5. በአሸባሪው ትህነግ እና ተላላኪዎች ጭምር በውሸት ሀገርን ለማፍረስ የሚያደርጉትን ተግባርና እኩይ ሴራ ለማጋለጥ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
  6. ሁላችንም የተቋማችንን እና የአከባቢያችንን ሰላም እና ጸጥታ ዘብ ሆነን ለመጠበቅ ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
  7. በተቋማችን የተሰጠንን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት፤ ከመንግስት የስራ ሰዓት ውጭ ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡
  8. የሀሰት የመረጃ ምንጮችን ላለመጠቀም እና እውነተኛ መረጃን ለማሰራጨት ቃል እንገባለን፡፡
  9. ሃገራችን በምትፈልገን በማንኛውም አይነት ተልዕኮ ለመሰማራት ዝግጁ መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡