የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙ ሁለት አረጋውያን ላይ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን በጎበኙበት ወቅት የተናገሩት ነው፡፡ በድሬዳዋ ከተማ የሚገኙ የአሰገደች በጎ አድራጎት ድርጅት እና ዳዊት የአረጋውያን በጎ አድራጎት ድርጅት በከተማው ጧሪ ቀባሪ ያጡ አቅመ ደካማ አረጋውያንን በመንከባከብ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ድርጅቶች ናቸው፡፡
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት ድርጅቶቹ ለአቅመ ደካማ አረጋውያን እያደረጉት ያለው እንክብካቤ ለማየት በመቻላቸው መደሰታቸውን በመግለፅ ለአገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያን እድሜያቸው ሲገፋና አቅማቸው ሲዳከም እንዳገለገሉ እቃ መጣል የለባቸውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አክለውም መንግስት ለአረጋውያን እየሰጠ ያለው ትኩረት ከፍተኛ ነው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር ጠ/ሚኒስትሩም ለአረጋውያን እያደረጉት ያለው ድጋፍ ምን ያህል ትኩረት እንደተሰጠው አመላካች ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ድርጅቶቹ አቅመ ደካማ አረጋውያን ወድቀው እንዳይቀሩ ሰብስበው በማቆየታቸው ምስጋና ይገባቸዋል በማለት ይህን ጥሩ ስራ ቀጣይነት እንዲኖረው ባለስልጣኑም በሀሳብም ሆነ በቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ አሰገደች የበጎ አድራጎት ድርጅት በ1980 ዓ.ም በአንድ ትንሽ ቤት ውስጥ ሁለት አረጋውያንን በመንከባከብ የተጀመረ ሲሆን ድርጅቱ አሁን ላለበት ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ ውጣ ውረዶችን ማሳለፉን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዘኸኝ ወርቁ ገልፀውልናል፡፡ አሰገደች የበጎ አድራጎት ድርጅት ዓላማ አድርጎ የተነሳው ጧሪ ቀባሪ ያጡ አረጋውያንን መንከባከብ፣የምግብ እና የጤና አገልግሎቶችን መስጠት ሲሆን አሁን ላይ በድርጅቱ 90 እንዲሁም ቤት ለቤት እንክብካቤ የሚደረግላቸው 20 አረጋዊያን መኖራቸውን አብራርተዋል፡፡ ዳዊት የአረጋውያን በጎ አድራጎት ድርጅትም በ1998 ዓ.ም ከኤጀንሲው ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡
የድርጅቱ መስራች አቶ ዳዊት በማዘር ትሬዛ ድርጅት ውስጥ ለረጅም ዓመታት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት ልምድ ያላቸው መሆኑን በመግለጽ የራሳቸውን ድርጅት ለማቋቋም መሰረት የሆናቸው አንድ ጎዳና ላይ የወደቁ አረጋዊን ለመርዳት ካላቸው ፍላጎት የመነጨ መሆኑን ስራ አስኪያጁ አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡ ዳዊት የአረጋውያን በጎ አድራጎት ድርጅት በአንድ አረጋውያን የተጀመረ ቢሆንም በአሁን ወቅት ከሁለት መቶ በላይ ለሆኑ አቅመ ደካማ አረጋውያንን የመንከባከብ፣ የምግብ እና የጤና አገልግሎቶችን በመስጠ ላይ መሆኑን ለመመልከት ተችሏል፡፡ ዳዊት የአረጋውያን በጎ አድራጎት ድርጅት ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ ሙሉ ወጪውን የሚሸፍነው የድሬደዋ ከተማ ህብረተሰብና መስተዳደሩ ሲሆን ምንም አይነት ድጋፍ ከውጪ እንደማያገኝ አቶ ዳዊት ገልፀውልናል፡፡ በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ እንዳሉት ድርጅቶቹ ለአቅመ ደካማ አረጋውያን እያደረጉት ያለው እንክብካቤ ለማየት በመቻላቸው መደሰታቸውን በመግለፅ ለአገር ባለውለታ የሆኑ አረጋውያን እድሜያቸው ሲገፋና አቅማቸው ሲዳከም እንዳገለገሉ እቃ መጣል የለባቸውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አክለውም መንግስት ለአረጋውያን እየሰጠ ያለው ትኩረት ከፍተኛ ነው ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር ጠ/ሚኒስትሩም ለአረጋውያን እያደረጉት ያለው ድጋፍ ምን ያህል ትኩረት እንደተሰጠው አመላካች ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ድርጅቶቹ አቅመ ደካማ አረጋውያን ወድቀው እንዳይቀሩ ሰብስበው በማቆየታቸው ምስጋና ይገባቸዋል በማለት ይህን ጥሩ ስራ ቀጣይነት እንዲኖረው ባለስልጣኑም በሀሳብም ሆነ በቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚያደርግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡